Thursday, October 15, 2015

በዓለ ጥምቀት በጎንደር ከተማ

ጥር 12 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዲ/ን ዘአማኑኤል አንተነህ /ከጎንደር ማእከል/
img 3695ቤተ ክርስቲያን በዓለ ጥምቀትን የምታከብረው የበዓሉን ጥንታዊነት በጠበቀ መልኩ ሲሆን፤ ሀገራችን በዓለም እንድትታወቅና የበርካታ ጎብኝዎች መስሕብ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ እንደመታደል ሆኖ ጎንደር ደግሞ የሊቃውንት መፍለቂያ ከመሆኗም በተጨማሪ ጥምቀት በድምቀት ይከበርባታል፡:

የ2007 ዓ.ም. አከባበሩም የሚከተለውን ይመስል ነበር፡-

Wednesday, October 14, 2015

አድርሽኝ

ነሐሴ 5 ቀን 2007 ዓ.ም
ምንጭ፡ ማኅበረ ቅዱሳን 
http://eotcmk.org/site/-mainmenu-24/--mainmenu-26/1953-2015-08-11-05-46-55
በዘአማኑኤል አንተነህ/ከጎንደር ማእክል/
፩.ታሪክ
20አድርሽኝ ታሪካዊ አመጣጡ በጎንደር ከነገሡት ነገሥታት መካከል ከ1703-1708 ዓ.ም ለአምስት ዓመታት በንግሥና የቆዩት ከዐፄ ዮስጦስ ጀምሮ ነው፡፡ አድርሽኝ የተሰኘው ሥርዓትም በእርሳቸው ተጀምሯል፡፡

ዐፄ ዮስጦስ የአድያም ሰገድ ኢያሱ የእህት ልጅ ፣ የፃድቁ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ናቸው፡፡ አባታቸው ደጃዝማች ድል በኢየሱስ ይባላሉ፣ እናታቸው በውል አይታወቁም፡፡ ዐፄ ዮስጦስ የጎንደር ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያንን የተከሉ እና በጥምቀት ጊዜ እመቤታችን የተገለፀችላቸው ንጉሥ ናቸው፡፡ ዐፄ ዮስጦስ በንግሥናቸው ወቅት ከሱዳኖች ጋር በነበራው ግንኙነት ሱዳኖች አንገብርም እያሉ ያስቸግሯቸው ነበር፡፡

ቱርኮች እና ግብጾች እየመጡም ሱዳኖችን አትገብሩ እያሉ ይሰብኳቸው ነበር፡፡ በአብርሃ ወአጽብሐ ዘመነ መንግሥት ሱዳኖች አንገብርም እያሉ በነበረበት ወቅት አብርሐ ወአጽብሐ ሒደው 5000 ግመል አመጡ እየተባለ ይነገርላቸዋል፡፡

በዐፄ ዮስጦስ ንግሥና ዘመንም ሱዳኖች አንገብርም በማለታቸው ንጉሡ ቸር አድርሰሽ ድል አድርጌ የመለስሽኝ እንደሆነ በየዓመቱ እዘክራለሁ ብለው ተስለው (ብጽዓት ገብተው) ወደ ጦርነቱ ሄዱ፡፡ ድል አድርገው ከተመለሱ በኋላ ሱባኤ ፍልሰታን ማታ ማታ መኳንንቱን ሰብስበው መዘከር ጀመሩ፡፡ ስያሜውንም €œአድርሽኝ€ በማለት ሰየሙት፡፡

• 50 የአቋቋም ደቀመዛሙርት ተመረቁ

ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም.
ምንጭ፡ ማኅበረ ቅዱሳን http://eotcmk.org/site/-mainmenu-18/1995-2015-09-18-18-35-44
ዲ/ን ዘአማኑኤል አንተነህ / ከጎንደር ማዕከል/
gonder beata 01በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በጎንደር ከተማ በደብረ ኃይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የአቋቋም ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ 50 ደቀ መዛሙርት ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመረቁ፡፡

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሀገረ ስብከቱ የመምሪያ ሓላፊዎች፣ የአብነት መምህራን እና ምእመናን የተገኙ ሲሆን፤ ደቀ መዛሙርቱ ከብፁዕነታቸው እጅ የአቋቋም ምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ “አዝመራው ብዙ ነው ሠራተኛው ግን ጥቂት ነው” በሚል ርዕስ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተው ለተመራቂ ደቀመዛሙርቱ በተማሩት ትምህርት ወንበር ዘርግተው በማስተማርና ለምእመናን ትምህርት ወንጌልን በመስጠት በተለይም ለገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን በመድረስ የተጣለባቸውን አደራ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በገዳማት እና በአብነት ት/ቤቶች ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

ሐምሌ 10 ቀን 2007 ዓ.ም.
ምንጭ፡ ማኅበረ ቅዱሳን http://eotcmk.org/site/-mainmenu-18/1935-2015-07-17-18-27-35
ከጎንደር ማእከል
በማኅበረ ቅዱሳን ጎንደር ማእከል በቅዱሳት መካናት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል አዘጋጅነት ‹‹ዘላቂ ልማት ለገዳማት እና ለአብነት ት/ቤቶቻችን›› በሚል መሪ ቃል በጎንደር ከተማ ሲኒማ አዳራሽ ሐምሌ 4 ቀን 2007 ዓ.ም የውይይት መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡

ጉባኤው ቅዳሜ ከሰዓት 8፡00 ላይ የተጀመረ ሲሆን፤ ጉባኤውን የከፈቱት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በመክፈቻ ንግግራቸው የአብነት ት/ቤቶቻችን የማንነታችን መገለጫና የሀገሪቱ የሊቃውንት መፍለቂያ ማኅፀን እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

የጎንደር ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ የአዲስ ዓመት በዓልን ከነዳያን ጋር አከበረ

መስከረም 7 ቀን 2008 ዓ.ም
ምንጭ፡ ማኅበረ ቅዱሳን http://eotcmk.org/site/-mainmenu-18/1995-2015-09-18-18-35-44
ዲ/ን ዘአማኑኤል አንተነህ /ከጎንደር ማእከል/
01nedayነገርግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው ወንድሙንም የሚያስፈልገውን ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?፡፡1ኛ. ዮሐ. 3፡17

መንፈሳዊ በዓላትን መንፈሳዊ ይዘታቸውን ጠብቆ ከማክበር ባለፈ የተቸገሩ ወገኖችን ማስታወስና መጎብኘት ሃይማኖታዊ ግዴታ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያናችን ለዘመናት ስትሰብክ ኖራለች ወደፊትም ትቀጥላለች፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑም ይህንን መሠረት በማድረግ በየበዓላቱ ነዳያንን በመጎብኘት፤ አብሮ በዓላትን በማክበር ችግሮቻቸውን በመጋራት ድጋፍ ያድርጋል፡፡

ለምን ነጭ ነጠላ እንለብሳለን ?

መስከረም 14ቀን 2008 ዓ.ም
ምንጭ፡ ማኅበረ ቅዱሳን http://eotcmk.org/site/-mainmenu-24/---mainmenu-27/2002-2015-09-25-06-33-41
ዘአማኑኤል አንተነህ
አባቶቻችን  መንፈሳዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረተ ሐሳቦች ላይ በመመሥረት ነጠላን እንለብስ ዘንድ ሥርዐትን ሠሩልን::111111111111111111
1.ጌታን አብነት በማድረግ
ጌታ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል የምሥጢር ሐዋርያት የሚባሉትን ጴጥሮስን ፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ወጥቶ ደቀ መዛሙርቱ እያዩት ልብሱ ነጭ ሆኖ ነበር፤"በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።"(ማቴ17:2) እኛም ሊያድነንና አርአያ ሆኖ ሊያስተምረን ሰው የሆነውን ጌታችንን አብነት በማድረግ ነጭ ነጠላን ለብሰን የደብረ ታቦር ምሳሌ ወደሆነችው ቤተክርስቲያን እንሰባሰባለን።