ከጎንደር ማእከል
በማኅበረ ቅዱሳን ጎንደር ማእከል በቅዱሳት መካናት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል አዘጋጅነት â¹â¹ዘላቂ ልማት ለገዳማት እና ለአብነት ት/ቤቶቻችንâºâº በሚል መሪ ቃል በጎንደር ከተማ ሲኒማ አዳራሽ ሐምሌ 4 ቀን 2007 ዓ.ም የውይይት መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
ጉባኤው ቅዳሜ ከሰዓት 8፡00 ላይ የተጀመረ ሲሆን፤ ጉባኤውን የከፈቱት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በመክፈቻ ንግግራቸው የአብነት ት/ቤቶቻችን የማንነታችን መገለጫና የሀገሪቱ የሊቃውንት መፍለቂያ ማኅፀን እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
ለዚህ መርሐ ግብር መካሄድ መነሻ የሆነው በየወሩ በመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ቅዱሳን በጎንደር ማእከል በቅዱሳት መካናት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል የሚዘጋጀው â¹â¹ዜና ገዳማትâºâº የተሰኘው መርሐ ግብር ነው፡፡
በዜና ገዳማት መርሐ ግብር በርካታ ፕሮጀክቶች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ሲሆን፤ ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት ምን እናድርግ በሚል 5 አባላት ያሉት ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡ ኮሚቴውም ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመነጋገር ሰው በመመደብና በጋራ በመሥራት ይህን የውይይት መርሐ ግብር አዘጋጅቷል፡፡
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በገዳማት እና አብነት ት/ቤቶች ዙሪያ በሰጡት የወንጌል ትምህርት ኅብረተሰቡ ኃላፊነት ተሰምቶት ለገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ትኩረት በማድረግ መጠበቅ፣ ማገዝና መንከባከብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
አቶ ጌትነት መኳኳንት በጎንደር ማእከል የቅዱሳት መካናትና ማኀበራዊ አገልግሎት ሰብሳቢ â¹â¹ወቅታዊ የገዳማት እና አብነት ት/ቤቶች ሁኔታâºâº የሚል የዳሰሳ ጥናት በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ባሉ አድባራትና ገዳማት ዙሪያ የተሠራ ጥናት አቅርበዋል፡፡ ገዳማት እና የአብነት ት/ቤቶች የኢትዮጵያውያን የአእምሮ ውጤቶች ለሚባሉት ሁሉ ምንጮች፤ የተማረ የሰው ኃይል መገኛዎች፣ ሀገርን በጸሎት ጠባቂ እና የሀገር መሪዎች እንደሆኑ በጥናቱ ተካቷል፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ የአብነት ተማሪዎች መሠረታዊ ችግሮች ያላቸውንም ተመልክቷል፡፡ እነዚህም፡-
የምግብ እጦት፤ የአልባሳት ችግር፤ የመጠለያ አለመኖር፤ የመብራት፣ ውኃ እና መጸዳጃ አገልግሎት ችግር፤ የመምህራኑ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ መሆን፤ የጤና ችግር፤ የተሐድሶ መናፍቃናን እንቅስቃሴ፤ ወዘተ መሆናቸው ገልጿል፡፡
ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ምን እናድርግ?â በሚል የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅÂ ሊቀ አእላፍÂ ቀለመወርቅ አሻግሬ፣ የአቢሲኒያ ባንክ እንኮየ መስክ ጎንደር ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ብሩህ ተስፋ፤ አቶ ጌትነት መኳንንት ውይይቱን መርተዋል፡፡ በውይይቱም ከቤቱ በርካታ የመፍትሄ ሓሳቦች ከተሰጡ በኋላ በሀገረ ስብከት ደረጃ ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጡ 10 አባላት ያሉት ቋሚ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ â¹â¹ሰው የሚመሰገነው በሕይወቱ አንድ ጥሩ ነገር ሲያደርግ ሊሆን ይችላል፤ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ሁልጊዜ የሚሠራ በመሆኑ ቢመሰገን ያንስበታልâºâº ሲሉ ብፁዕነታቸው ተናግረዋል፡፡ የተመረጡት ሰዎችም ጠንክረው እንዲሠሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ውስጥ 86 ገዳማት፣ 605 አድባራት፣ 1697 የገጠር አብያተ ክርስቲያናት፣ 21859 ካህናት፣ 16724 ዲያቆናት እና 1774 የአብነት መምህራን ይገኛሉ፡፡
|
No comments:
Post a Comment