Wednesday, October 14, 2015

ለምን ነጭ ነጠላ እንለብሳለን ?

መስከረም 14ቀን 2008 ዓ.ም
ምንጭ፡ ማኅበረ ቅዱሳን http://eotcmk.org/site/-mainmenu-24/---mainmenu-27/2002-2015-09-25-06-33-41
ዘአማኑኤል አንተነህ
አባቶቻችን  መንፈሳዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረተ ሐሳቦች ላይ በመመሥረት ነጠላን እንለብስ ዘንድ ሥርዐትን ሠሩልን::111111111111111111
1.ጌታን አብነት በማድረግ
ጌታ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል የምሥጢር ሐዋርያት የሚባሉትን ጴጥሮስን ፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ወጥቶ ደቀ መዛሙርቱ እያዩት ልብሱ ነጭ ሆኖ ነበር፤"በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።"(ማቴ17:2) እኛም ሊያድነንና አርአያ ሆኖ ሊያስተምረን ሰው የሆነውን ጌታችንን አብነት በማድረግ ነጭ ነጠላን ለብሰን የደብረ ታቦር ምሳሌ ወደሆነችው ቤተክርስቲያን እንሰባሰባለን።
2. ቅዱሳንን አብነት በማድረግ
22222222222222222
በዮሐንስ ራእይ ምእራፍ 6 ላይ በዐጸደ ነፍስ ስላሉ ቅዱሳን የሚከተለው ተጽፎ ይገኛል:: "አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ። ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።"(ራዕ.6፡9-11)
በራእይ ሰባትም ባለራእዩ እንዲህ ብሏል፡፡ "ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤" (ራዕ.7:9)እኛም ቅዱሳኑን አብነት በማድረግና ከበጉ ቀኝ ነጭ ለብሰን የመቆም ተስፋን በመሰነቅ ነጭ ነጠላን እንለብሳለን።

3.መላእክትን አብነት በማድረግ
ጌታ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው በለየ በሦስተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ወደ መቃብሩ በሔደች ጊዜ የጌታ ትንሣኤን የሚያበሥሩ ሁለት ነጭ የለበሱ መላእክትን አግኝታ ነበር፦ "ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች።" (የዮሐንስ ወንጌል 20:12) እኛም ቅዱሳን መላእክትን አብነት በማድረግ ነጭ ለብሰን የትንሣኤያችን ማእከል በሆነች ቤተ ክርስቲያን እንሰባሰባለን።

4. ክርስትና በሰማያዊ ተስፋ የተሞላ ብርሃናማ ሕይወት ነውና ይህን ተስፋችንን በማሰብ ነጭ ነጠላን እንለብሳለን። ስለዚህ መስቀልያ አጣፍተን መስቀሉን በማሰብ የምንለብሰው ነጠላ እንዲሁ በዘፈቀደ የሚለበስ አለመሆኑን በመገንዘብ ሥርዐቱን ልንተገብር ይገባል።

1 comment: